ቤተ-መጻሕፍት አጠቃቀም | አማርኛ (Amharic)

የህዝብ ቤተመፃህፍት ማለት ምንድነው?

መጻህፍት ለማግኘት፣ ኮምፑተር ለመጠቀም፣ በነጻ ኢንፎርሜሽን መማርን ያጠቃልላል። ከቤተመጻህፍት ወደ ቤት ወስደው መጠቀም ይችላሉ ግን ከተጠቀሙበት በሃላ ወደ ቤተመጻህፍት መመለስ ኣለብዎት። ይህንን ለመጠቀም ግን የቤተመጻህፍት ካርድ ያስፈልግዎታል።

የሲፎልስ ወይ የሚነሃሃ ካውንቲ ነዋሪ ከሆኑ የቤተመጻህፍቱ ካርድ በነጻ ነው።

የቤተመጻህፍት ካርድ እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

 • መታወቂያ ወረቀት፣ መንጃ ፈቃድ፣ፓስፖርት፣ግሪን ካርድ ማምጣት
 • ኣድራሻዎ ሰው የላከልዎት ፖስታ ካለ ወይም የቤት ወይ ኪራይ ውል በማምጣት
 • የቤተመጻህፍቱ ሰራተኛን ለእርዳታ ይጠይቁ

ምን ለመጠቀም ችላለሁ?

 • መጻህፍት
 • ፊልም ወይም የተሌቪጅን ትእይንት
 • መጽሔቶች
 • የቦርድ ጨዋታዎች
 • የሙዚቃ ሲድዎች
 • የልጆች መጫወቻዎች

ለምን ያህል ጊዜ መጠቀም እችላለሁ?

መጻህፍት, መጽሔቶች, የቦርድ ጨዋታዎች, ሙዚቃ ሲዲዎችና ,የልጆች መጫወቻዎች, ፊልም (03) ለሶስት ሳምንት

ኣዲስ ፊልም ለሶስት ቀናት(03) 

በምን ቋንቋ የተጻፉ መጻህፍቶች መጠቀም እችላለሁ?

ብዙ መጻህፍቶች በስፓንሽ በራሻይኛ የተጻፉ ለእንግልዝኛ መማርያ የሚረዱ ኣሉን

በቤተመጻህፍት ሌላ ነገሮች ምን ማድረግ እችላለሁ?

 • ኮምፑተር መጠቀም
 • ፎቶ ኮፒና ህትመት ጥቁርና ነጭ ከሆነ ኣስር ሳንቲም በቀለም ከሆነ ሃያ ኣምስት ሳንቲም
 • ፋክስ ሃያ ኣምስት ሳንቲም
 • ቅኝት
 • ዳውንሎድ ወይም ማስታለፍ መጽሃፍም ሆነ ፊልም ወደ የእርስዎ መሣሪያ
 • የጆሮ መከላከያና ማዳመጫ ኣንድ ዶላር

መቼ ነው ቤተመጻህፍቱ የሚከፈተው?

የትኛው ቤተመጻህፍት በኣቅራብያዬ ይገኛል?